
የመንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ግለሰብ ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን፣ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህንን እሴት በተግባር ለማሳየትና ለማበረታታት የተዘጋጀው የመንገድ ደህንነትና የእውቅና መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።
በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አካባቢ፣ በኪ.ሜ 29 በሚገኘው ታፍ ኢነርጂስ ስማርት ስቴሽን የተካሄደው የመንገድ ደህንነትና የእውቅና መርሃ ግብር የታፍ ሆልዲንግ ከህብረት ኢንሹራንስ፣ከመድህን ኢንሹራንስ እንዲሁም ከቡና ኢንሹራንስ ጋር በመተባበር “ደህንነት ምርጫ ሳይሆን ኃላፊነት ነው” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አክብረውታል። በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ ታላላቅ የመንግስትና የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ክቡራን እንግዶች፣ የየታፍ ሆልዲንግ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።

ከተገኙት ክቡራን እንግዶች መካከል፦
1. የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ
2. የEthiopian Reinsurance S.C. (Ethio-Re) ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ
3. የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ETRE) ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናስር አባሲመል
4. ሻምበል/ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ
5. የቡና ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳኛቸው መሃሪ
6. የሕብረት አኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሰረት በዛብህ
7. የመድህን ኢንሹራንስ የክብር ተወካዮች
8. የታፍ ኢነርጂስ መስራች አቶ አክሊሉ ዘለቀ
9. የታፍ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተንሳይ አክሊሉ
“የዋና ሥራ አስኪያጁ የአቶ ተንሳይ አክሊሉ መልዕክት “
በመርሃ ግብሩ ወቅት የታፍ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተንሳይ አክሊሉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የድርጅቱ ስኬት በተቋሙ ውስጥ በሚሰሩ ሰራተኞች ትጋት፣ ኃላፊነትና የጋራ ትብብር ላይ እንደሚገነባ አስታውቀዋል።በተለይም ደህንነትን ማስቀደም የድርጅቱ የሥራ ባህል አካል መሆኑንና፣ በየዕለቱ በኃላፊነት የሚሰሩ ሰራተኞችን ማድነቅና እውቅና መስጠት የታፍ ሆልዲንግ ቁልፍ እሴት መሆኑን አጉልተዋል።
“የምናከብረው ውጤት የአንድ ሰው ሳይሆን የብዙዎች ትጋት፣ ኃላፊነትና የጋራ ጉዞ ውጤት ነው። ደህንነትን በማስቀደም፣ ልህቀትን በማበረታታትና በጋራ በመስራት የበለጠ ስኬት እናስመዘግባለን።”
በመርሃ ግብሩም 10 የታፍ ሆልዲንግ ስር የሚገኙ ድርጅቶች የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በመንገድ ደህንነትና የላቀ የሥራ አፈፃፀም ላሳዩት ብቃት ከሜዳሊያ እስከ ዋንጫ ድረስ ተሸልመዋል።

በተያያዘም፣ የታፍ ሆልዲንግ ዓመታዊ የሰራተኞች ክብረ በዓል ተከብሮ፣ በየድርጅቶቹ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የዓመቱ ምርጥ ፈጻሚዎች ተሸልመዋል። ይህ መርሃ ግብር የታፍ ሆልዲንግ ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን ዋጋ፣ ለልህቀት ያለውን እውቅና እና ለመንገድ ደህንነት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ ታላቅ አጋጣሚ ነበር።
ደህንነትን ማስቀደም፣ ልህቀትን ማክበር እና ስኬትን በጋራ ማክበር — የTAF Holding ጉዞ ይቀጥላል!
